የእንደጋኝ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለእንደጋኝ ወረዳ የጀነ/ታዳጊ ማዘጋጃ የከብት በረት አጥር ግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የእንደጋኝ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ለእንደጋኝ ወረዳ የጀነ/ታዳጊ ማዘጋጃ የከብት በረት አጥር ግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾን ከዚህ በታች ያለው መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።
መስፈርት
1/ ተጫቶች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉና ፈቃቸውን ያደሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
3/ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/VAT/ ተመዝጋቢ የሆነና የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸው
4/ ተጫራቾች አጠቃላይ እቃ አቅርቦ የሚሰሩ መሆኑ መታወቅ አለበት።
5/ የታከስ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
6/የጨረታ ሰነድ ከግዢ እና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ።
7/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 10000 /አስር ሺ ብር/ በእንደጋኝ ወረዳ ፋኢል ዕ/ቤት ስም በማሰራት ከኦርጂናል የጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይኖርባታል ።
8/ተጫራቾች በአላይን የተመዘገቡና የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፤
9/መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው/ያላት
ተጫራቾች የምትወዳደሩበትን ዋጋ በሚነበብ የእጅ ፅሁፍ በመሙላት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ኮፒና አንድ ኦርጅናል በተለያየ ፖስታ በማሸግ በላዩ ላይ ኮፒ እና ኦርጂናል መሆኑን በመፃፍ ሶስቱም በአንድ እናት ፖስታ በመጨመር በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት በኋላ 8:00 ሰዓት ግ/ክ/ን/አስተዳደር ስ/ሃደት ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታው ሳጥን በ8:00 ታሽጎ በዚሁ አለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተኙበት 8፣30 ሰዓት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
➢ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
መረጃ፡- በስልከ ቁጥር 011 350 00 47/46
ጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት (ድንቁላ)
