Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ ባለ 14፣ ባለ 16 እና ባለ 20 ሎት 02 የተለያዩ የአትክልት ዘሮች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ ለአትልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም ዳይሬቶሬት አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የችግኝ ማፍያ ላስቲክ ባለ 14ባለ 16 እና ባለ 20 ሎት 02 የተለያዩ የአትልት ዘሮች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1.     በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ

2.     የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3.     የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ. 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::

5.     የሚገዙ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲ እና አትክልት ዘር ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

6.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁጥር ለሎት 01 ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት 02 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) እና በቅድመ ሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditonal Bank Guarantee) ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው ማንኛውም ተጫራች የጨረታ /የመወዳደሪያ/ ሃሳቡን የቴኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናንሽያል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጂ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናቸውን ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ለተጠየቁት ግዥዎች ናሙናዎችን ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡

8.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16 ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4:00 ታሽጎ 430 ይከፈታል።

9.     /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10. በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582205849 /0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

11. ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል፡፡ ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት፡፡

12. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ

 

የአማራ ራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ

Save Tender