Tender Detail

Tender Details


የወ/ሮ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ለትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮዎች አገልግሎት የሚውል 1. የህንፃ መሳሪያ እቃዎች 2 የአውቶ እቃዎች 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች 4. የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎች 5. የጽህፈት መሳሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወ/ ስኂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 . ለትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ለቢሮዎች አገልግሎት የሚውል 1. የህንፃ መሳሪያ እቃዎች 2 የአውቶ እቃዎች 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች 4. የኮምፒዩተር ተዛማጅ እቃዎች 5. የጽህፈት መሳሪያዎች አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሱ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር200.00 (ሁለት መቶ ብር)በመግዛት መወዳደር ትችላላችሁ::

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

4. የግዥው መጠን 1 200,000.00 ከሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርወረቀት ማቅረብ ሚችሉ፣

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፉ ከላይ በተ. 1- 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6 የሚገዙትን የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ለት መቶ ብር/ በመክፈል ከወ/ ስኂን ፖሊቴከኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 204 /አዲሱ ህንፃ / ማግኘት ይቻላል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክበተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የከፈሉበትን ማስረጃ መያዝ አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ መከፈቻ ዕለት ኦርጅናል ንግድ ፈቃድና ቫት ሰርቲፊኬት የግብር መከፈያ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሲጠየቁ ማሳየት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 1130 ሰዓት ድረስ

በወ/ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 204 አዲሱ ህንፃ በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 400 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

ሳጥኑም በዚህ ሰዓት ይታሻል በዚሁ ቀን 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡

10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር204 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-10-10 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፤

የወ/ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender