ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ሥራዎችን ማሰራት ይፈልጋል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 34/2018፣ 35/2018፣ 36/2018 እና 37/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
1. ለጎንደር ከተማ ዘመናዊ ቄራ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የአልሙኒየም በር እና መስኮት አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 34/2018
2. ለባህር ዳር ገቢዎች፣ለደሴ አሚኮ እና ለግዳን ሆስፒታል ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ ጅአርፒ፣ ፓዮነር ታንከር፣ ፋየር ፓንፕ እና ዋተር ፓምፕ አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 35/2018
3. ለደሴ አሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ የኤሌከትሮ መካኒካል (Äር System) አቅርቦት እና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 36/2018
4. ለዋንዛየ ሎጅ ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውልጅብሰም ቦርድ አቅርቦት እና ገጠማ ጨረታ ቁጥር 37/2018 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ | የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመሳተፍ የታከስ ክሊራንስ ያለው/ያላት፤
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 ምድር ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት እና ለዳታና ቴሌ አቅርቦትና ገጠማ ስራ ለ15 ተከታታይ ቀናት እንዲሁም ለሊፍት 20 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከላይ በተጠቀሰው ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል። የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፦
ባህር ዳር-058-218-0538/ 09-18-01-06-17 / 09-18-71-66-16/ 09-21-26-13-00/ 09-21-25-89-20
አዲስ አበባ ፡- ስልክ ቁጥር 011 126 5338/ 09-20-24-93-20/ 09 11-90-86-29
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
