አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር የሚያገለግል ላፕቶፕ እና ዲስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር: AWACH/NCB/G/02/2026/2018
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር የሚያገለግል ላፕቶፕ እና ዲስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ተጫራቾች፡-
1.በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉ እና ከገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2.በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/በመክፈል አዋሬ, ሴቶች አደባባይ በሀብትሽ አውቶሞቲቭበሚያስገባው ታጥፎ አድዋ ድልድይ የሚወስደው መንገድ አጋርሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6.ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ኮምፒውተሮች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7.በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸውና ፊርማቸውን እንዲሁም _ የድርጅቱን _ ማህተም አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8.ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች Manufacturer Authorization Form (MAF): An original authorization letter from HP, issued on HP letterhead, explicitly authorizing the bidder to supply 30 units of the specified model to Our SACCO.
9.በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
10. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
11. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-557-7341 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- አዋሬ፣ ዜማ ፈርኒቸር ገባ ብሎ፣ አጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201
አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃላ/የተ/ር መሠ/የህ/ስ/ ማህበር ዋና ቢሮ
