Tender Detail

Tender Details

  • Company Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115572949
  • Websitehttps://aacaprac.gov.et/?lang=ahm
  • Deadline26 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-02-26 00:00:00
  • Categories Gardening And Landscaping , Wood And Wood Working , Forest And Tree Sales

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የእንጦጦ ፓርክን በአገር በቀል እጽዋት መተካት ስለፈለገ በውስጡ የሚገኙ የባህር ዛፎችን በቁማቸው በመሸጥ ይፈልጋል።


የባህር ዛፍ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን የእንጦጦ ፓርክን በአገር በቀል እጽዋት መተካት ስለፈለገ በውስጡ የሚገኙ የባህር ዛፎችን በቁማቸው በመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ባህር ዛፎቹን ቆርጦ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

1.     ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።

2.     የባህር ዛፎቹን ለማንሳት በቂ አቅም፣ ልምድ እና የዛፍ ማስወገጃ መሳሪያ ያለው እንዲሁም ለአገር በቀል እጽዋቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ የሚያደርግ።

3.     አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በአርባ አምስት ቀን ውስጥ ስራውን መጨረስ የሚችል።

4.     የተቆራረጡ ቅርንጫፎች ከፓርኩ ውስጥ በራሱ ትራንስፖርትና የጉልበት ሰራተኛ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የሚችል።

5.     ዛፉ ከተቆረጠ በኋላ ድጋሚ እንዳያበቅል / እንዳያቆጠቁጥ ዲባር ማድረግ የሚችል።

6.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7.     ዛፉ በሚወገድበት አካባቢ ሊደርስ የሚችል መሰረተ ልማት ጉዳት ማስተካከያ የሚውል የጨረታውን ከጠቅላላው መነሻ ዋጋ ሁለት በመቶ ሲፒኦ ማሰያዝ የሚችል።

8.     ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ መገናኛ ዘፍመሽ ፊት ለፊት ታሜጋስ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።

9.     ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ፋይናንሺያል ዶክመንትና ቴክኒካል ዶክመንት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በአለው 11ኛው ቀን ጠዋት 400 ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዚያው ቀን ጠዋት 430 መገኛኛ ዘፍ መሽ ፊት ለፊት ባለው ታሜ ጋስ ህንጻ ላይ ሶስተኛ ፎቅ በግዢ እና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።

11. አሸናፊው ከተለየ በኋላ በሶስት ቀን ውስጥ ስራ መጀመር የሚችል።

12. አንድ ተጫራች ከሁለት ኮምፓርትመንት በላይ መጫረት አይችልም።

13. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣይ ሰኞ ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

14. ዘግይቶ የደረሰ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

15. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 09 12 47 56 09 / 09 10 85 13 75 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን

Save Tender