Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-221-7002
  • Website
  • Deadline13 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-03-13 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በዳራ አትልቾ ወረዳ ተፈሪ ኬላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሊያሠራ ላቀደው ሁለት የመማሪያ ብሎኮች ቀሪ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ 2018 በጀት ዓመት በዳራ አትልቾ ወረዳ ተፈሪ ኬላ 2 ደረጃ /ቤት ሊያሠራ ላቀደው ሁለት የመማሪያ ብሎኮች ቀሪ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት፡-

1.     ደረጃቸው GC 6/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2018 ዓም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።

2.     አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።

3.     በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

4.     የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።

5.     የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና BANK GAURANTEE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

6.     የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና .ዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7.     የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

8.     የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 26ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 እስከ 600 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 600 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 800 ሰዓት ላይ ይከፈታል፤ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም።

10. አሠሪው /ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ (ሀዋሳ ከተማ)

Save Tender