Tender Detail

Tender Details


የጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ በREDD+ ፕሮጀክት ድጋፍ የደንና የፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት አገልግሎት የሚውል ፕላስቲክ ቱዩብ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጋምቤላ ///መንግስት የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ REDD+ ፕሮጀክት ድጋፍ የደንና የፍራፍሬ ችግኝ ዝግጅት አገልግሎት የሚውል ፕላስቲ ቱዩብ ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤

በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

1.     ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2.     ተጫራቾች በመ/ቤቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በጋምቤላ ከተማ በሚገኘው የክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸውና የዘመኑን እንቅስቃሴ የሚያመለክት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

4.     ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ለሚጫረቱበት 1% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤

5.     ተጫራቾች የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6.     የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘው የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አርጅናልና ኮፒ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤

7.     ጨረታው ሠነድ ማስገቢያ ሣጥን 16 ቀን ከጠዋቱ 300 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቅጥር ግቢ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።

8.     የጨረታ ሠነድ ማስገቢያ ቦታ ጋምቤላ ከተማ በክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 02 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

9.     ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 0475512977 ይጠቀሙ፤

 

የጋምቤላ //// የእርሻና ተፈጥሮ ልማት ቢሮ

Save Tender