ድርጅታችን 3/ሶስት/ የተለያዩ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን የ3ቱንም ቢሮዎች የጥበቃ ሥራ በአስቀጣሪ ድርጅቶች /ኤጀንሲዎች/ አማካኝነት ማሠራት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በትምህርት፣ በጤና፣ በወጣት ልማት ዘርፍና በችግረኛ ቤተሰብ የገቢ ማስገኛ ስራ ላይ በመሰማራት ከተለያዩ መንግስታዊ ሴክተር መ/ቤቶችና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባባር በርካታ የልማት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ አገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅታችን 3/ሶስት/ የተለያዩ ቢሮዎች ያሉት ሲሆን የ3ቱንም ቢሮዎች የጥበቃ ሥራ በአስቀጣሪ ድርጅቶች /ኤጀንሲዎች/ አማካኝነት ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት የጥበቃ ሠራተኞችን ለድርጅቶች በማቅረብ በቂ እውቀትና ልምድ ያላችሁ፣ በአመቱ የታደሰ የሥራ ፍቃድ ያላችሁ እና ከዚህ ቀደም ተመሣሣይ ሥራ ስለመስራታችሁ የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07/ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ክፍለ- ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በመገኘት የምታቀርቡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል።
አድራሻችን ክፍለ-ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ - ስልክ +251 99 623 0927 / +251 94 910 1110
አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት
