የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጉለሌ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ሚስማር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጉለሌ አካባቢ በሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ እና መጋዝን የሚገኙትን የተለያዩ ዕቃዎች (ሚስማር፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የማባዣ ማሽኖች፣ ቴሌቪዥኖች፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እና ሌሎችም ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጉለሌ በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከየካቲት 16/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3) ማንኛውም ተጫራች ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 27 2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።
4) ጨረታው ጉለሌ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን የካቲት 27 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋስትና በ3 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
6) ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።
7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 91 047 4668 ወይም 251 91 156 9913 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
