በሰሜን ሸዋ ዞን የዘመሮ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት በከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የተለያዩ ማሽኖች ማለትም ግሪደር፣ እስካቫተር፣ ሮሎ፣ ሻወር ትራክ እና ሲኖ ትራክ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በሰሜን ሸዋ ዞን የዘመሮ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት አመት በከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የተለያዩ ማሽኖች ማለትም ግሪደር፣ እስካቫተር፣ ሮሎ፣ ሻወር ትራክ እና ሲኖ ትራክ መከራየት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም በከተማው ውስጥ የመንገድ መብራት ለማዘርጋት ፓውዛ፣ አንፖልና ከዚሁ ጋር ተያያዥ የሆኑ የኤሌክትሪክ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያለውና ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
1. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ያላቸው፤ የሚጫረቱት ጨረታ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።፡
5. የሚያቀርቡትን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፤
7. የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ሆኖ በ15ተኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት በCPO ወይም ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለጸ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት የውል ማስከበሪያ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት
10. አሸናፊ የሚለየው በሎት በጥቅል ዋጋ ስለሆነ ሁሉንም መሙላት አለባቸው፡
11. ማንኛውም ወጭ፣ ብልሽት፣ በራሱ ወጪ ሸፍኖ መሥራት የሚችል፡፡
12. የሚያቀርቡት እቃ /ማሽን/ እና የሚገነቡት ግንባታ ጥራት ብቃት ያለው መሆን አለበት፡፡
13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ሆኖ በ15ተኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ግን 16ኛውቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዘመሮ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ግ/ፋ ቡድን
