የደ/ምዕ/ ሸዋ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት በ 2018 በጀት አመት አዲስ ላስገነባው G+5 ህንጻ ለ2ኛ ዙር የወጣ የተለያዩ ጥራታቸው የተጠበቁ ሎት አንድ: ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት ሁለት: የጂም እቃዎችን ከአገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር BuEJWBG/O3/2018
የደ/ምዕ/ ሸዋ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት በ 2018 በጀት አመት አዲስ ላስገነባው G+5 ህንጻ ለ2ኛ ዙር የወጣ የተለያዩ ጥራታቸው የተጠበቁ ሎት አንድ: ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት ሁለት: የጂም እቃዎችን ከአገር ውስጥ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች አሟልተው መገኘት ይኖርባቸዋል።
1. በንግድ ዘርፉ ወይም መስኩ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣
2. የመንግስት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ወቅታዊ ማስረጃ፣
3. በመንግስት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱና የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችል፣
4. በጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተወዳዳሪው ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ቢያንስ እስከ 10,000,000.00 /አስር ሚሊዮን ብር/ እና ለጂም ዕቃዎች እስከ 5,000,000.00 /አምስት ሚሊዮን ብር/ መሆን አለበት፡፡
5. ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ 150,000.00 ብር (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለሎት ሁለት 80,000.00 ብር (ሰማንያ ሺህ ብር) ሕጋዊ ከሆነ ባንክ የተረጋገጠ CPO ከሚያቀርቧቸው ሰነዶች ጋር ማያያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በደ/ምዕ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የቢሮ ቁጥር 16 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ሰነድ እና የቴክኒክ ሰነድ በአንድነት አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የካቲት 27/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለፀው ቦታ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች በተቀመጠው እስፔስፊኬሽን እና ካታሎግ መሰረት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. አሸናፊው ባሸነፈባቸው ጠቅላላ እቃዎች ላይ 10% አሥር በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ማሸነፉ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ በደ/ምዕ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በመገኘት ውል መፈረም ይኖርበታል።
11. ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ውል የማይፈፅም አሸናፊ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ የሚደረግ ሆኖ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
12. በጨረታው ውል መሠረት እቃዎቹን በሙሉ ካስረከበ ክፍያው ወዲያው ይፈፀማል።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር 011 366 46 34/ 011 366 48 42
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት /ወሊሶ/
