በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨ.ሰ.ቁ፡-NCB‐ AAMMI-004/2018
በኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዲስትሪ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ለቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
· ሎት-1 ዲስክ ቶፕ ኮምፒውተር
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ያህል ሰነዱን አዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ።
⁕ ተጫራቾች ከሚያቀርቡት እቃ ጋር ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፊቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የግብር ክሊራንስ / ጨረታ ለመሳተፍ የሚስጥ/የሚያስችል ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
⁕ ተወዳዳሪዎች በጨረታው ላቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተጫራቹ ምርጫ ከሚከተሉት ዓይነቶች አንዱ ሊሆን ይችላል።
(ሀ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣
(ለ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ የባንክ ጋራንቲው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፣
⁕ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስራ ቀን) የስራ ቀናት በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በግዢ ክፍል ቢሮ ቁጥር 014 በመገኘት ሰነዱን በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለፀው አስተሻሸግ መሰረት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
⁕ ጨረታው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዳማ የግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የስብሰባ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም። ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 022 111 0689 / 09 12 26 46 80 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዳማ ከወንጂ ማዞሪያ ተቃራኒ አቅጣጫ 500 ሜ ላይ ስልክ፡- 022 111 0689 / 09 12 26 46 80
ፋክስ:- 022 1111866
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የአዳማ ግብርና ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
