የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በ2018 ዓ.ም ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ለቡናና ደን ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ፓሊቲን ቲዩብ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት በ2018 ዓ.ም ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ለቡናና ደን ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውሉ ፓሊቲን ቲዩብ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ፈቃድ ያለው፡፡
2. ለአቅራቢነት የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
4. የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር ያለው፡፡
5. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የግብር ከፋይነት ማስረጃ የሚያቀርብ፡፡
6. የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ መግዛት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 20,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን 1 ኦርጅናል ፋይናሻል እና የቴከኒካል በ2 ኮፒ በአንድ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፒ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት 8፡00 ሰዓት የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ቡና፤ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ባለስልጣን ግዥ ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 02 ተጫራችቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ግዥ ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት፡፡
በስልክ ቁጥር፡- 0462122897 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቡና፤ ፍራፍሬና ቅመማቅመም ባለስልጣን
