ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የፓወር ፋክተር ኮሬክተር እንድናስገጥም አቅጣጫ ሰጥቶናል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የፓወር ፋክተር ኮሬክተር እንድናስገጥም አቅጣጫ ሰጥቶናል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች የፓወር ፋክተር ኮሬክተር ለመግጠም የጥናት አናሊሲስ በመስራት የእቃው ዋጋ እና የሙያው ዋጋ ከነ ሙሉ ዕቃው በማቅረብ ሥራውን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሸናፊው ድርጅት ውል አስሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. ተጫራች አናሊሲስ ለመስራት በድርጅቱ ሰው ኃይል አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማሽኖቹን ጥናት ፋሲሊቲ ሰርቪስ በተገኙበት መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራች የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርፍትኬት ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20(ሃያ ሺህ) በይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ስም ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርበታል።
4. ተጫራች ከዚህ በፊት በዚሁ ሥራ በጨረታ የተሳተፈባቸው ድርጅቶች (መ/ቤቶች) የመልካም የሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነዱ ፋይናንሻል እና ቴከኒካል ለየብቻ ለይቶ በማሸግና በኤንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት በመግለፅ ክብ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ተጫራች ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡
7. በጨረታ ማስታወቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦቹን ያሟሉ ተጫራቾች ብቻ ወደ ፋይናንሻል ግምገማ ያልፋሉ፡፡
8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው /በስድስተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው /በስድስተኛው የሥራ ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይሆናል።
10. ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር - 12
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- የቢሮ 0115 580 129 / 0115 576 954/
ሞባይል - 0922 079 575 / 0911 397 239
ይሓ ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
