በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኮዋሽ ፕሮግራም ድጋፍ በሁለት ሎት፤-ሎት 1፡- ለወተራ ቀጨማ መሃል አንበርብር አንደኛ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ሎት 2፡- ወሻ ሶያማ ቀበሌ ገበያ ቃል-ሕይወት መንደር 01 የንፅህ ውሃ መጠጥ መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ የተቆፈረውን ወደ ሶላር ፓምፕ ፓኔል ለመቀየር እና ፓምፕ ሶላር ኮንትሮለርና
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በኮዋሽ ፕሮግራም ድጋፍ በሁለት ሎት፤-ሎት 1፡- ለወተራ ቀጨማ መሃል አንበርብር አንደኛ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ሎት 2፡- ወሻ ሶያማ ቀበሌ ገበያ ቃል-ሕይወት መንደር 01 የንፅህ ውሃ መጠጥ መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ የተቆፈረውን ወደ ሶላር ፓምፕ ፓኔል ለመቀየር እና ፓምፕ ሶላር ኮንትሮለርና አክሰስሪ፣ ከብልዎችና አክሰስሪ ዕቃዎች ለማቅረብ፣ ስትራክቸር ትራንስፖርት አገልግሎትና እንስታላዘሽን ሥራ ለማስሠራት ሕጋዊ ተጫራቾችን ማለትም ኤሌክትሮ መካኒካል ሥራ ዘርፊ የተሰማሩ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ፤
1. የሥራ ፈቃዳቸው በሶላር ፓምፕ አክስሰሪና ኤለክትሮ መካኒካል ሥራ የተሰማሩ ተጫራቾች 2018 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም የታደሠ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)ተመዚጋብ እና የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆንአለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
3. የጨረታ ማስከበሪያ (BID SECURITY) ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GAURANTEE) ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበረያ ተቀባይነት የለውም፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ወንዶ ገነት ወረዳ ገብዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ በመያዝ ከወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የሥራው ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
6. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከብረያ (BID SECURITY) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስምንተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ወንዶ ገነት ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ፤የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያግደውም፡፡
8. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ካላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
10. አሸናፊ ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅደመ-ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን የወንዶ ገነት ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
