በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት1፡- የዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ጥገና ፣ ሎት 2፡- የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ሴክተር መምሪያ መፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የህንፃ/ጥገናና መፀዳጃ ቤት ግንባታ/ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት1፡- የዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ጥገና ፣ ሎት 2፡- የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ሴክተር መምሪያ መፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች በግንባታ ዘርፍ BC/GC -7(ሰባት) እና ከዚያ በላይ የሆነ
2. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. ከግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
4. ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸዉ፤
6. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
7. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣
8. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር ለሎት1፡- የዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ጥገና ጥገና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2፡- የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ሴክተር መምሪያ መፀዳጃ ቤት ግንባታ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክበተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምርያ በማለት ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ተጫራቾች ስለጨረታዉ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በማሸግ እና በጥቅል በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ መቅረብ አለበት፡፡
11. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም አርጅናል እና ኮፒ የሚል ጽሁፋ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
12. የጨረታው ማስታወቂያው በወጣ 21ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በሚመጡበት ግዜ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ ቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የማይመለስ ኮፒ ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባቸዋል መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣
ሚዛን አማን
