በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ3ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የፅሕፈት እቃዎችን፣ በሎት 2 የተለያዩ የፅዳት እቃዎችን፣ በሎት 3 የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን እንዲሁም በሎት 4 የኤሌክትሮኒክስና የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት በ3ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የፅሕፈት እቃዎችን፣ በሎት 2 የተለያዩ የፅዳት እቃዎችን፣ በሎት 3 የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን እንዲሁም በሎት 4 የኤሌክትሮኒክስና የጄኔሬተር መለዋወጫ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው
1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፣
5. የዘመኑ ግብር የከፈለ ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች/ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው የድርጅቱን ማኅተምና ፈርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራች የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፋ ድምር ከተሠራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት።
9. ተጫራች የአንድ ዋጋ ከሞላ በኋላ ወደ ጎን አባዝቶ እና ወደ ታች ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
10. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ እየሆነ ይመረጣል።
11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለ እና ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻ ሦስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት። በዚህ መሠረት ሦስቱም ፖስታዎች ለየብቻ ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
13. ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ልክ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ C.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
14. የጨረታ አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 % በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ CPO ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
15. የጨረታ ሰነዱን ከማሠልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በሥራ ቀንና ሰዓት ከ25/06/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 06/07/2018 ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ7/07/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። በዚሁ ቀን 7/7/2018 ዓ/ም ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የዕቃ አቅርቦት ትዕዛዝ መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ጥራቱን አረጋግጦ ማስረከብ አለበት። የጥራት ኮሚቴው ካልተቀበለው ቀይሮ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ክፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ሕጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሬጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት።
19. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
20. ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፋ 20% የመቀነስም ሆነ 20% የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
21. በዚህ ማስታወቂያው ያልተገለፁ ሌሎች ሕጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ መሠረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል። ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በሥራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።
የብርሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት
