የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት አዲስ አበባ በርበሬ ተራ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ የሞዴል ዲስትሪክት ግንባታ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት አዲስ አበባ በርበሬ ተራ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ የሞዴል ዲስትሪክት ግንባታ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የኮንትራክተሮች ምዝገባ የምስክር ወረቀት (የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ) ያለውና GC/BC 3 እና በላይ የሆነ ፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ የአቅራቢዎች ዝርዝር፣ እና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደለት/ክሊራንስ ያለው፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የድርጅቱ ግዥ ቡድን በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ዶክመንቶችን ኦርጂናልና ኮፒ በተለያዩ በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲያቀርቡ እናሳስባለን፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ስራ ቀን ይከፈታል።
ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእድሳት ስራ አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial lnputs Development Enterprise) ስም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 130,000.00 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺ) ከጨረታው ቴክኒካል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ አዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከከሊፋ ህንፃ በስተሰሜን የባቡር ሀዲዱን ተሻግሮ ወደ አራት መንታ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ) ቢሮ)።
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0111-57-24-97 ይደውሉ ወይም በአካል መጎብኘት ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብአቶች ልማት ድርጅት
