የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
v የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
v የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
v የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
v በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
v በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
v የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶክሜንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል
v ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000 (አስር ሺህ) ብር CPO (ሲ.ፒ.ኦ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል
v አሽናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ C.RO (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል
v ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩከ፤ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሽፍኖ ዕቃውን ማሰረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ዳይረክቶሬት ቢሮ አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
v መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
v አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ ማጫረት አይችልም
v የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገነዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት ቀጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል።
v ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0462125731 እና 09119746687 እና ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ
