በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የምዕራብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ሚኒባስ የኪራይ አገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
አ/አ/ከ/አስ/ቤ/ል/ኮ/ምዕራብ ቅ/ጽ/ቤት 08/2018
1. መ/ቤታችን በአዲስ አበባ ክልል ውስጥ ሆኖ በተለያዩ መስመሮች የሚገኙትን ሠራተኞች ጠዋት እና ማታ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ አቃቂ ቃሊቲ ከሚገኘው ጽ/ቤታችን ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን ቅዳሜ ግማሽ ቀን የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ) ሚኒባስ የመጫን አቅም ከ2-5 ሰው የሆኑ ታክሲዎች የኪራይ አገልግሎት የግዥ መለያ ቁጥር ምዕራብ 08/2018
2. በግልፅ ጨረታ ሀገር ውስጥ ተጫራቾችን አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥዎችን መፈፀም ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
3. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰና ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ ወረቀት፤ የባለቤትነት ሊብሬ መታወቂያ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ቁጥር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና በዘመኑ የታደሰ ሶስተኛ ወገን የመድን ሽፋን ማቅረብ የሚችል ጨረታ ለመሳተፍ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
4. የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡት መኪናዎች ሲበላሹም ሆነ የሰርቪስ ጊዜያቸው ሲደርስ ኮድ 3 የሆኑ የኪራይ መኪናዎችን መተካት የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
5. ጨረታውን መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አቃቂ ቃሊቲ የኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ከሚገኘው ጽ/ቤታችን መግዛት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/CPO/ቢድ ቦንድ ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሂሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ስልክ ቁጥር 0912117915 ወይም 0931804871 ይደውሉ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
