በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ በጀት አማካኝነት ጋቢዎን እና የጋቢዎን ማሰሪያ ሽቦ እቃዎች ግዥ እና የጎርፍ መከላከል ሥራ ለማሰራት ኤክስካቫተር መከራየት ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ያልተማከለ የአደጋ ስጋት ቅነሳ በጀት አማካኝነት፡-
· ጋቢዎን እና የጋቢዎን ማሰሪያ ሽቦ እቃዎች ግዥ
· በይምለዎ ቀበሌ መንጠር ወንዝ እና በሆራ ቀበሌ ደረቄ ወንዝ የጎርፍ መከላከል ሥራ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ ኤክስካቫተር መከራየት የሚፈልግ ሲሆን መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት መሰረት በማድረግ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን-
1. በዘርፉ የተመዘገበ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ (የማሽነሪ አከራይ የንግድ ስራ ፍቃድ) የግብር ከፋይመለያ ቁጥር እና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከሰ ከፋይነት መረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጋቢዎን እና ለጋቢዎን ማሰሪያ ሽቦ 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ እና ለማሽን ኪራይ 50,000 /አምሳ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ማስያዝ እንደሚጠበቅባቸው ይኸውም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፅ/ቤታችን ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብራችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ወቅት እንዲገኙ አይገደዱም ነገር ግን በጨረታው መገኘት አለብን ብለው ካሰቡ መገኘት ያለበት አካል የተጫረተው ባለቤት ወይም ህጋዊ ውከልና ያለው አካል ኦርጅናል የውክልና ማስረጃውን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከኤ/ግ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የሚከፈል ብር ለጋቢዎን እና ለጋቢዎን ማሰሪያ ሽቦ 500 /አምስት መቶ ብር/፣ ለማሽን ኪራይ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ፡፡
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማለትም ከ5/እስከ 19/7/2018 ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን ማለትም በ20/7/2018 ከጠዋቱ 4:00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
7. ተጫራቾች ለወሰዱት የተጫራች መመሪያ /የጨረታ ሠነድ/ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ጨረታው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው አሸናፊ ስለሚሆን እያንዳንዱን የዋጋ መሙያ ሙሉ በሙሉ ጨረታው ላይ መሞላት አለበት ይህ ካልሆነ ግን ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
9. ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
10. ተጫራቾች የተጠየቁትን ኤክስካቫተር ማሽኖች ስፔሲፊኬሽናቸውን መሰረት ያደረገ ሊብሬ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የኤ/ግ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
