የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሞተር ሳይክል (Motor Cycle) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MSF/LP/03/2026
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ጥቅል አንድ፡ ሞተር ሳይክል (Motor Cycle)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለአንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር (150,000.00) የሚሆን በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሲፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 19 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በዕለቱ መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 19 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር
0115-505607, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባደ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
