በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በጀት አመት ከፌዴራል ሮድ ፈንድ በተገኘ የበጀት ድጋፍ በሚጢቆሎ ቀበሌ፤ ሜጃ ቀበሌ፤ ሸዋበር ቀበሌ፤ ቦርቸሌ ቀበሌ፤ ቀዲዳ ቀበሌ፤ አንቻሮ መስመርእና አየር ማረፊያ ቀበሌ ለሚያሠራው ነባር መንገድ ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት፡-1 (አንድ) እንዲሁም ከ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በ2018 በጀት አመት ከፌዴራል ሮድ ፈንድ በተገኘ የበጀት ድጋፍ በሚጢቆሎ ቀበሌ፤ ሜጃ ቀበሌ፤ ሸዋበር ቀበሌ፤ ቦርቸሌ ቀበሌ፤ ቀዲዳ ቀበሌ፤ አንቻሮ መስመር እና አየር ማረፊያ ቀበሌ ለሚያሠራው ነባር መንገድ ጥገና ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት፡-1 (አንድ) እንዲሁም ከከተማ አስተዳደሩ በተገኘ የበጀት ምንጭ (ድጋፍ) ለሚያከናውነው በሁሉም ክፍለ ከተሞች ውስጥ የመንገድ ግንባታ እና ከፈታ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎችን እና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዢ በሎት፡-2 (ሁለት) መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
4. መ/ቤቱ ምንም አይነት ቅድመ ከፍያ አይከፍልም ስለሆነም ተጫራቾች ይሄንን ታሳቢ አድርገው መሙላት አለባቸው።
5. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ብር የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በማስላት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዢያ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለበት።
6. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በሚጠይቀው የዋጋ አሞላል ብቻ መሙላት አለበት። በሚጠይቀው ዋጋ አሞላል ካልሞሉ የጨረታ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
8. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በሎት /በጥቅል/ ድምር ውጤት ስለሆነ የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም ያልተሞላ አይተም ከተገኘ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 ማግኘት ይችላሉ።
10. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10/7/2018 ዓ.ም እስከ 24/7/2018 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት በግዥና/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 25/07/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
12. ጨረታው ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 508 በ 25/07/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ 4፡30 ላይ ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻልን። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ለበለጠ መረጃ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን መ/ቤት አምስተኛ ፎቅ ቢ/ቁጥር 508 በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 351 33 37/033 551 05 04 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ- ሁሉም ተጫራቾች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ፈርሞ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት።
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለሥልጣን
