የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፈዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply, Install, Test and Commission Ground Water borehole drilling & construction ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/38/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፈዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply, Install, Test and Commission Ground Water borehole drilling & construction ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የቃውን ዓይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Supply, Install, Test and Commission Ground Water borehole drilling & construction |
ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ግንባታ |
DCES/SF/38/2026 |
መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት |
መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡45 ሰዓት |
100,000.00 |
ስለሆነም-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ አሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከኢዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail Info@dce-et.com
የድረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
