በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ለጤና ጣቢያችን የወረቀት አልባ ስራ ለማስጀመር የ(Network Infrastructure for Health centers) ወይም የኔትወርክ ዝርጋታ እቃዎችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡- 03/2018
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡- ለጤና ጣቢያችን የወረቀት አልባ ስራ ለማስጀመር የ(Network Infrastructure for Health centers) ወይም የኔትወርክ ዝርጋታ እቃዎችን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመግዛት እና ማሰራት እንፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ልታሟሉ የሚገቧቸው መስፈርቶች:-
1. በመስኩ ህጋዊ ሰነድ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖራቸው በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ፈርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን መፃፍ ሲኖርባቸው በተጨማሪም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጉ/ክ/ወ/4 ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403/409 ፋይናንስ ክፍል ቀርቦ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ስርዝ ድልዝ የሌለው ዋጋ በመሙላት በ10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በእለቱ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በ 11ኛው ቀን 4፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ነገር ግን ባይገኙም የጨረታ ሣጥኑን ከመክፈት አንደናቀፍም፡፡
3. የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 70,000 ብር ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. የተጠየቁ ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ትክክለኛ ናሙና ወይም ስፔስፍኬሽን (Specification) ፎቶ ግራፍ፣ ካታሎማ ወይም ማንዋል ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ8ኛው ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጥ/በቀ/ጤ/ጣ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በግንባር በመቅረብ ወይም የድርጅቱን ውክልና እና መታወቂያ በያዘ ግለሰብ ውል መዋዋል ሲኖርባቸው ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለውን አማራጭ ይወስዳል፡፡
6. ተጫራቶች ለሚጫረቱት ዕቃ ትክክለኛውን ብራንድ (ዓይነት) ናሙና እና የዕቃ መግለጫ (Specification)፣ ካታሎማ ወይም ማንዋል፣ የእቃው ፎቶ ግራፍ ማቅረብ እና መስሪያ ቤቱ ከቀረበው ስፔስፊኬሽን ጋር አንድ መሆን ሲኖርባቸው ጨረታው ጥራትን እና ዋጋን መነሻ አድርጎ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
7. ተጫራቾች ንብረቱን በራሳቸው ትራንስፖርት እና የጉልበት ዋጋ በመክፈል ይዘው በመቅረብ ስራውን መስራት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. መ/ቤቱ በጨረታ ላይ ከተጠቀሱት እቃዎች ብዛት ላይ 25% ጨምሮ ከአሸናፊ ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በመሆኑም የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ/ ብር ይሆናል፡፡
አድራሻችን፡- ጉ/ክ/ከ/ወረዳ 4 ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ ልዩ ስሙ ከቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተ- ክርስቲያን በ1ኛው መንገድ ከቤተ ክርስቲያኑ 400 ሜትር ከፍ ብሎ።
ለተጨማሪ ማብረሪያ፡- ጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ በግንባር በመቅረብ ወይም ስ.ቁ
0111-11-13-96፣ 011-1250172 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የጥበብ በቀጨኔ ጤና ጣቢያ
