Tender Detail

Tender Details


በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኘው ለመንገድ ትራንስፖርት ከቀበሌዎች ጋር የሚያይዝ የመንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ቁጥር 004/2018

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኘው ለመንገድ ትራንስፖርት ከቀበሌዎች ጋር የሚያይዝ የመንገድ ጥገና ስራ ለማሰራት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1.       የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN /ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2.       የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

3.       በኮንስትራክሽን ዘርፍ G ስራዎች ደረጃ 6 ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች የታደሰ የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4.       ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው ርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

5.       ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 22ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዢ ቢሮ .3 ከጠዋቱ 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

6.       ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

7.       ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግንባታውን ዓይነት፣ ዝርዝር መግለጫ፣ ስራ ዝርዝር፣ እና መመሪያ /ሰነድ ከመ/ቤታችን ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ።

8.       ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ግንባታ 60,000/ስልሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ትእዛዝ CPO ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ/መሂ1 ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9.       /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጪ /ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

10.   በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 011-119 0350 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 011-119 0270 / 280 +251 99 704 1395 በመደወል ወይም Telegram channel@t.me/Ensarowereda  ወይም Gmail አካውንታችን ensaroweredafinanceoffice@gmail.com መላክ ይችላሉ።

አድራሻ- ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 . ከደብረ ብርሃን 83 .

 

የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን/

Save Tender

Hibir Construction Corporation Procurement Reference No.

READ MORE