በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ፤ በምስራቅ ሸዋ ድስትሪክት እና እንጦጦ ጫንጮ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OFWE/BA-04/2018
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ፤ በምስራቅ ሸዋ ድስትሪክት እና እንጦጦ ጫንጮ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
በፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ፤ ምስራቅ ሸዋ ድስትሪክት እና እንጦጦ-ጫንጮ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1. የጊንድላ፣ የአጣና፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ/ አጠገብ በሚገኘው የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።
2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የወጣበትን ቀን ጨምሮ/ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
3. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ/ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።
4. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- WWW.oromiaforest.et ማግኘት ይችላሉ
በስልክ ቁጥር 0111 24 02 49 መደወል ይችላሉ።
የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት
