Tender Detail

Tender Details


በጉ/ክ/ከ/ወ/10 የሸጐሌ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ/ም 3ኛዙር በግልፅ ጨረታ ለመጫረት ይፈልጋል ለጤና ጣቢያው የሚያስፈልጉ እቃዎች ሎት 1 Network infrastructure Digitalization ዕቃዎች እና ሎት 2 የአጥር ስራ (Fence Work) ሎት 3 ቋሚ የህክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል።


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ///03/2018

 

በጉ////10 የሸጐሌ ጤና ጣቢያ 2018 / 3ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ለመጫረት ይፈልጋል ለጤና ጣቢያው የሚያስፈልጉ እቃዎች ሎት 1 Network infrastructure Digitalization ዕቃዎች እና ሎት 2 የአጥር ስራ (Fence Work) ሎት 3 ቋሚ የህክምና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፦

1.     ከሚገዛው ዕቃ አገልግሎት/ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /በዌብ ሳይት የተመዘገቡ ተጫራቾች ከዌብሳይቱ ላይ ፕሪንት አድርገው ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3.     በግዥ አዋጁ መሠረት ጥቃቅንና አነስተኛ እራሳቸው በሚያመርቱት ምርት ላይ የምናበረታታ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡

4.     ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(CPO) የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ የሎት 1 20,000 ብር ሎት 2. 10,000 ሎት 3. 10,000 የሚያሲዙ ሲሆን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያሲያዙትን CPO ዋናውን ወይም ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዙ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡

6.     ተቋማችን የሚገዛቸውን የአገልግሎት/ የዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በሎት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል 4 ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 401 መግዛት ይችላሉ

7.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት በአንድ ወጥ በታሸገ ኦርጅናል ፖስታ እና በታሸገ ኮፒ ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8.     /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ያላካተተ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጐ የማያቀርብ፣

9.     ስርዝ ድልዝ ያደረገ እና አማራጭ ጨረታ የተጠቀሙ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

10. የጨረታው ሣጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 1130 ታሽጎ በማግስቱ በስራ ቀን ጠዋት 300 ሰዓት ተጫራቾች / ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጥራት ለመለየት የሚያስችል በፎቶ ሳምፕል ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት 4 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 401 በሚገኘው ግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ በፎቶ ሳምፕል ያላቀረበ ተወዳዳሪ/ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።

12. ቋሚ ዕቃዎች በተመለከተ ግን ደረጃና ጥራታቸውን የሚገልፅ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡

13. የተጫራቾች አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

14. /ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ 20% /ሃያ ከመቶ/ ጨምሮም ቀንሶም መግዛት ይችላል፡፡

15.ጨረታው /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ሸጐሌ አንበሳ ጋራዥ አጠገብ ስልክ ቁጥር 0112 59-24-26/0112737447 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሸጎሌ ጤና ጣቢያ

Save Tender