የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ለድምጽ አሰጣጥ ሥልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/12/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ለድምጽ አሰጣጥ ሥልጠና እና የኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ምድብ አንድ- ለድምጽ አሰጣጥ የሥልጠና ቁሳቁስ ስርጭት የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
ምድብ ሁለት- ለድምጽ አሰጣጥ ኦፕሬሽን ቁሳቁስ ስርጭት የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ
1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ሥራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስክ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል _ በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ፣-
ለምድብ አንድ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ከoo/100)
ለምድብ ሁለት ብር 150,000.00 (ብር አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ከoo/oo) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
6. ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል በተለያየ ፖስታ በማሽግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
7. ጨረታው መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
8. ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር +251 115153468
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ
