Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ከ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

በጉለሌ ከ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሎት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

የሎቶች እና የጨረታ ዋስትና መጠን

  1. ሎት 1 – የደንብ ልብስ - 4,000 ብር (አራት ሺህ ብር)
  2. ሎት 2 – የጽሕፈት መሣሪያ – 4,550 ብር (አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ብር)
  3. ሎት 3 – የተለያዩ ሕትመቶች — 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
  4. ሎት 4 – አላቂና ቋሚ የሕከምና ዕቃዎች - 5000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
  5. ሎት 5 – ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች – 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
  6. ሎት 6 – ኤሌክትሮኒከስና ሕንፃ መሣሪያዎች – 500 ብር (አምስት መቶ ብር)
  7. ሎት 7 – ቋሚ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) – 2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)
  8. ሎት 8 – (የጀነሬተር ጥገና፣ ፍራጅ፣ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ላፕቶፕ – 4,250 ብር (አራት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር)
  9. ሎት 9 - ስፌት - 2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)
  10. ሎት 10 – ትራንስፖርት — 1000 ብር (አንድ ሺህ ብር)
  11. የህንጻ ጥገና ፕላንት ቁሳቁስ – 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
  12. ሎት የካፌ አገልግሎት – 6000 (ስድስት ሺህ ብር)
  13. ሎት የአንቡላንስ ጥገና – 2000 (ሁለት ሺህ ብር)

የጨረታ ተሳታፊዎች መስፈርቶች

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TN Number) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ከሀገር ውስጥ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው። እንዲሁም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑ፣ ከደረጃቸው አካል የተሰጠ በሚሠሩት ሥራ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል፣ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በግዥ የሥራ ሂደት፣ 4ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 50 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ለሚያቀርቡባቸው ዕቃዎች በተናጠል ኦርጅናል እና ኮፒውን በመለየት፣ በታሸገ ኢንቨሎፕ የሚጫረቱበትን የዕቃ ዓይነት በመጥቀስ፣ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 50 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት በጉለሌ ከፍለ ከተማ እንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ ስም በባንከ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ መሆን አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዕቃ ወይም ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ አለበት።
  8. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት በውል መሠረት በተቋሙ ንብረት ከፍል ገቢ ሲያደርግ ያስያዘው ገንዘብ ይመለሳል።
  9. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ፣ በከኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሥራ ቀናት በአዳራሸ ቁጥር 51 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ኮሚቴ ይከፈታል።
  10. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ መሥሪያ ቤቱ ከውል በፊት 20% የመቀነስ ወይም 20% ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። እንዲሁም ለካፌ ተጭራቾች ከስድስት ወር በፊት የዋጋ ማስተካከያ የማይደረግ መሆኑን እንገልጻለን። የቤት ኪራይና ውሃ መብራት ነጻ መሆኑን እንገልጻለን።
  11. ተቋሙ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አድራሻ:- ሸሮሜዳ 31 ቁጥር ባስ ማዞሪያ፣ 400 ሜትር ወደ እንጦጦ ማርያም በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ጉለሌ ከ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 1 ጽ/ቤት አጠገብ።

ስልክ ቁጥር፡ 011 154 0587 / 011 124 0272

በጉለሌ ከ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for procurement and installation of various consumable and fixed items for Entoto Fana Health Center, covering 12 lots including clothing, medical supplies, cleaning materials, furniture, electronics, printing, transport, and maintenance services. Bidders must hold valid licenses, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender