Tender Detail

Tender Details

  • Company Tis Isat Water Works PLC (የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ባህር ዳር ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-220-48-26
  • Websitehttps://www.tisisat.com/
  • Deadline14 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price
  • opening date2026-04-14 00:00:00
  • Categories Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የተለያዩ ጎማዎችን እና የማሽነሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የተለያዩ ጎማዎችን እና የማሽነሪ መለዋወጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

 

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ቀን

ሎት 1

የተለያዩ ጎማዎች

50,000.00

ከስቶክ

ሎት 2

የማሽነሪ መለዋወጫ

100,000.00

30 ቀን

 

ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል።

የተጫራቾች መመሪያ፤

1.     ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና TIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

2.     ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 930 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው /ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ C.P.O ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።

5.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።

6.     ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው

7.     ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።

8.     ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

9.     የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ 90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።

11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው /ቤት መሆን አለበት።

13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።

14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ።

 

ጢስ እሳት ውኃ ሥራዎች /የተ/የግ/ማህበር

Save Tender