ኩባንያችን ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ሳሪስ 106 ቅርንጫፍ መጋዘን የሚገኙ የተለያዩ የቫናይደር ስሪት የኤሌክትሪክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ሳሪስ 106 ቅርንጫፍ መጋዘን የሚገኙ የተለያዩ የቫናይደር ስሪት የኤሌክትሪክ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፣ ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍሎ በግዛት በጨረታ መሳተፍ ይችላል።
ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰአት ድረስ በአካል ተጫራቾች የሚፈልጉትን እቃ ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ፎርም ላይ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ ያቀረቡት 10,000 (አስር ሺህ ብር) CPO በማስያዝ የድርጅቱ ፋሲሊቲና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
በዚሁ የግዥ ጨረታ የሚቀርበው ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተሰጠው ሰንጠረዥ ብቻ ነው።
ጨረታው ከአስር ተከታታይ ቀናት በኋላ የሚኖረው የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋና መ/ቤት በሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
1. ለጨረታ የወጡ እቃዎች ጨረታ በገዙበት ሰነድ በመያዝ እቃው በሚገኝበት ሳሪስ 106 የድርጅቱ መጋዘን ማየት ይችላሉ።
2. የጨረታ አሸናፊዎች በማስታወቂያ ከተገልጹት ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ቫትን ጨምሮ በመክፈል እቃዎችን ማንሳት አለባቸው።
3. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው እቃዎቹን የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያው የተያዘው ገንዘብ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
4. የጨረታ ተሸናፊዎች የአሸናፊዎች ዝርዝር ከተገለጸባቸው ቀን ጀምሮ ለጨረታ ያስያዙት CPO ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
5. በአንደኛው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 0114-421133
የውስጥ መስመር 212 ወይም 223 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ አዲስ አበባ ደብረ ዘይት መንገድ (ሣሪስ አካባቢ)
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1116 አዲስ አበባ
ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር
