የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ከተለያዩ ክልሎች (ማዕከሎች) የምርጫ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ የጭነት ተሽከርካሪ የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የጭነት ተሽከርካሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NEBE/NCB/14/2018
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ለማስፈፀም ከተለያዩ ክልሎች (ማዕከሎች) የምርጫ ቁሳቁስ ማሰባሰቢያ የጭነት ተሽከርካሪ የኪራይ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቦርዱ ግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ማግኘት ይችላሉ።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሠርተፍኬት እና በመንግሥት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት መስክ ያላቸውን መልካም አፈጻጸም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታ ሰነዱን ከቦርዱ የግዥ አስተዳደር የሥራ ክፍል በመውሰድ ሞልተው አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (ብር አንድ መቶ ሺህ ከ00/100) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተወዳዳሪዎች ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ ሆኖ በአንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ሚያዝያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ቦርዱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- +251 115 15 34 68
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
