ኩባንያችን ጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች የመንገድ ስራ ንኡስ ኮንትራት (access road)፣ የዉሃ መርጫ (sprinklers) አቅርቦትና ገጠማ ስራ፣ የግንባታ ግብአቶች እና የሲሚንቶ ማጓጓዝ እንዲሁም የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች የመንገድ ስራ ንኡስ ኮንትራት (access road)፣ የዉሃ መርጫ (sprinklers) አቅርቦትና ገጠማ ስራ፣ የግንባታ ግብአቶች እና የሲሚንቶ ማጓጓዝ እንዲሁም የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃዉ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ/ ማጠናቀቂያ ጊዜ |
|
ሎት 1 |
የመንገድ ስራ ንኡስ ኮንትራት (access road) |
300,000.00 |
45 ቀናት |
|
ሎት 2 |
የዉሃ መርጫ (sprinklers) አቅርቦትና ገጠማ ስራ |
300,000.00 |
45 ቀናት |
|
ሎት 3 |
የግንባታ ግብአቶች |
100,000.00 |
30 ቀናት |
|
ሎት 4 |
የሲሚንቶ ማጓጓዝ |
100,000.00 |
እንደ አስፈላጊነቱ |
|
ሎት 5 |
ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች |
100,000.00 |
ከ30-45 ቀናት |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል።
የተጫራቾች መመሪያ፤
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምሰክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸዉን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸዉን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisis.com ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተዉን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል።
6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና ቴክኒካል ሰነዳቸዉን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR 03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀዉ መጠን 20% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊዉ ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
9. የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ 05 ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10% የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀዉ መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ዕቃዉ ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያዉ ጽ/ቤት መሆን አለበት።
13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ዉድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 / 058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 058 220 4830 መጠየቅ ይችላሉ።
ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
