Tender Detail

Tender Details


በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥገናዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 03/2018

 

በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ ቁጥር 1 የመጀመርያ ደረጃ /ቤት 2018 ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ጥገናዎች፡- የቅድመ አንደኛ ደረጀ ምድረ ጊቢ ተራዞ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ጊቢ አጥር በብረት የተማሪዎች ሽንት ቤት የመምህራን ሽንት ቤት የተማሪዎች የእጅ መታጠቢያ ቦኖ፣ የውሃ መስመሮች ዝርጋታ የሮቶ ጥገና እና እጥበት የተማሪዎች መማሪያ ክፍል በርና መስኮት ጥገና የኮምውተር፣ ፕርንተርና ፎቶ ኮፒ እና የጀነሬተር ሰርቪስ ለመስራት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸውቲን-ነምበር እና አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ አለባቸው።

2.     ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 9 እንቁላል ፋብርካ እምብልታ ሆቴል ከፍ ብሎ ከሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1 ደረጃ ቁጥር 1 /ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በየእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና በፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች እቃዎችን ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማችሁን ፊርማችሁና አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ//ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1 ደረጃ ቁጥር 1 /ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 1000 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት 11ኛው ቀን 400 በጄኔራል ታደሰ ብሩ 1 ደረጃ ቁጥር 1 /ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።

7.     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ ማሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

8.     የማወዳደሪያ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሞላት አለበት።

9.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

10./ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም 20% ከውሉ በፊት መቀነስ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

11./ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ እስከ 6 ወር ዋጋ ጭማሪ ሳይደረግ ተጨማሪ 25% ዕቃ ግዥ መፈፀም ይችላል።

12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበርያ ማስያዝ ይኖርበታል።

13. ተጫራቹ ያሸነፈውን እቃ የመ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት አምጥቶ ማስረከብ አለበት።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አምራች ከሆኑ ከአገር ውስጥ አቅርቦት ጋር በሚወደዳር ጊዜ 3% ልዩ አስተያየት ይደረግላቸዋል።

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 011 827 8952

 

በጉለሌ /ከተማ ወረዳ 9 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 1 ደረጃ ቁጥር 1 /ቤት

Save Tender