የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ከሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎች አንዱ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ሲሆን ለመቅደላ ወረዳ ለጠቢ የአፈር ግድብ ደለል ማውጣትና ጌት ቫልቭ ቅየራ ፕሮጀክት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ሀገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ከሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎች አንዱ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ሲሆን ለመቅደላ ወረዳ ለጠቢ የአፈር ግድብ ደለል ማውጣትና ጌት ቫልቭ ቅየራ ፕሮጀክት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፣
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣
3. በሙያው ፈቃድ WWC- WWGC/GWWC ያላቸው
4. ደረጃ 2 እና በላይ ፈቃድ ያላቸው
5. በ2018 ዓ.ም የሙያ ፍቃድ ያሳደሱ፣
6. የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
8. ተጫራቾች በኦሪጂናል ዕቃ መገንባትና እና ያሸነፉትን የግንባታ ማቴሪያል በባለሙያ ማስፈተሽ እና የጥራት ደረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. የሚገነባው ግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ጊዜ በአካል ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላከ መረጃውን (ኦርጅናል ፈቃዳቸውን) በመያዝ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 500,000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
13. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
14. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስዝ ይሆናል፡፡
15. ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር (በጠቅላላ በሎት ድምር) ነው፡፡
16. ጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሻል የሚገመገም ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቴክኒካልና ፋይናሻል ጨረታ ሰነዱን ለየብቻ በማሸግ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
17. ጨረታው ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
18. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033 111 61 34 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 81 18/19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
