Tender Detail

Tender Details

  • Company አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
  • Address ሰመራ ከተማ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-666-01-26
  • Websitehttps://afaredu.gov.et/am/
  • Deadline26 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-04-26 00:00:00
  • Categories Printed Advertising Materials , Printer And Photocopy Machine

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ6ኛ እና የ8ኛ) ክፍል ከልል አቀፍ ፈተናና ከፈተናዎች ጋር የተያያዘዙ የመልስ መስጫ ወረቀቶችና የሰርትፊኬት ህትመቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም በጀት አመት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (የ6ኛ እና የ8ኛ) ክፍል ከልል አቀፍ ፈተናና ከፈተናዎች ጋር የተያያዘዙ የመልስ መስጫ ወረቀቶችና የሰርትፊኬት ህትመቶችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1.     በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው።

2.     በተለይ በፈተና ህትመት በቂ ልምድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     የፈተናውን ደህንነት ለማስጠበቅ የደህንነት የጥበቃ አካል እና በካሜራ የታገዘ መሆን አለበት።

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ሠመራ ትም/ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ሀሳብ እና ዋጋ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ሰነዶችን በመለየት በ2 ኮፒ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርበቸዋል።

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(ቢድ ቦንድ) ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣

7.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

8.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ትምህርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ክፍል ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

9.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በትምርት ቢሮ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በ11ኛዉ ቀን በ3፡00 ሠዓት ይከፈታል።

10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 በስልክ ቁጥር 033-666-01-25/ በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

Save Tender