ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የድርጅታችን ንብረት የሆነውን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚገኝ ህንፃ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ሥራ ማከናወን ደረጃ 5 እና በላይ የሚችሉ የግንባታ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
Commercial Nomminees PLC
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/32/2018
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር የድርጅታችን ንብረት የሆነውን አፍሪካ ህብረት አካባቢ የሚገኝ ህንፃ የሴፕቲክ ታንክ ስላብ ሥራ ማከናወን ደረጃ 5 እና በላይ የሚችሉ የግንባታ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደስ የንግድ ፈቃድ፤ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የግንባታ ሥራውን የምታከናውኑበት ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-10:30) ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
