Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃ.የተ.የግ.ማህበር
  • Address ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116733497
  • Website
  • Deadline12 May 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-05-12 00:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለገማድሮ ቡና እርሻ ልማት የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EAC 030/2018

 

1.     ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ለገማድሮ ቡና እርሻ ልማት የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታ ሥራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሚያዝያ 20 ቀን 2018 . ጀምሮ እስከ ግንቦት 4 ቀን 2018 . ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 230- 630 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ 7:30 -1100 ሰዓት ድረስ ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎ አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው የታክስ ሊራንስ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት፡-

-       አንድ ዋና /Original የጨረታ ሰነድ ለብቻው በታሸገ ፖስታ፡፡

-       ንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ እንዲሁም፡።

-       ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት፡፡

-       በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

4.     ተጫራቾች የእንግዳ እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤት ግንባታን ስራ የጉልበት ወይም የሙያ የአገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም ኮንዲሽናል ባንክ ጋራንት ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 . እስከ ጠዋቱ 430 ሰዓት ድረስ በሮ ቁጥር 208 ሲሆን፤ ጨረታውን የመፈቻ ቀን ግንቦት 4 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል፡፡

6.     ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ያልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

7.     ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 0116676204 ፋከስ ቁጥር 0116732006 ደውለው መጠቀም ይችላሉ፡፡

8.     ኢትዮ አግሪ ሴፍት ኃላ/የተ/የግ/ማኅበር ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ኢትዮ አግሪ ሴፍት /የተ/የግ/ማኅበር

Save Tender