በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የሐራጅ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 006/ 2018
በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የማይሰጡ ዕቃዎችን የንብረት አስወጋጅ ኮሚቴ ከለዩት ዕቃዎች ውስጥ አንዱ የኤሌክትሪክ ኬብል ሲሆን እንዲወገድ ባቀረቡት መሠረት በግልጽ ሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ግለሰቦች የመንግሥት ተቋማት/
1. የዕቃው ዓይነት የኤሌክትሪክ ኬብል ነው።
2. ሽያጩ የሚከናወነው በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ንብረትነቱ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ነው።
3. አድራሻ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በወላይታ ዞን ሶዶ ግብርና ኮሌጅ በማርካቶ ከፍለ ከተማ ፋና ቀበሌ ነው።
4. የኤሌክትሪክ ኬብል ዓይነት 3*70*35 mm2 የሆነ ብዛት በጥቅል ከ400 ሜትር በላይ ነው። ነገር ግን ተጫራች የአንድ ሜትርን ዋጋ ይጫረታል።
5. ተጫራች ዕቃውን ለማየት የሚፈልግ ከሆነ እስከ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ድረስ በመቅረብ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየትኛውም በሥራ ቀን በሥራ ሰዓት ወደ ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ በመጠየቅና ማየት ይችላል።
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ15 ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው 16ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ዕቃው ባለበት ይካሄዳል። 16ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ይካሄዳል።
7. ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይጠበቅበታል። በሌላ አማራጭ የሚቀረብ ተቀባይነት የለውም።
8. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነትን በተቋሙ ሀላፊ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ሙሉ በሙሉ በግብርና ኮሌጅ አካውንት ገቢ ማድረግ እና ዕቃውን ማንሣት ይኖርበታል።
9. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስቁጥር 0465513984 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
በደ/ኢ/ክ/መንግሥት የግብርና ቢሮ የወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
