በዲላ ከተማ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት በUIIDP ፕሮግራም በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ በተለያዩ አካባቢ ለሚገነቡ የጎርፍ መሄጃ ቦይ ግንባታ እና የመንገድ መብራት ሪሎኬሽን (ቦታ መቀየር) በቀረበ ዝርዝር መሠረት ከዚህ በታች በተጠቀሱ አካባቢዎች ላይ ማስገንባት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በዲላ ከተማ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት በUIIDP ፕሮግራም በ2018 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ በተለያዩ አካባቢ ለሚገነቡ የጎርፍ መሄጃ ቦይ ግንባታ እና የመንገድ መብራት ሪሎኬሽን (ቦታ መቀየር) በቀረበ ዝርዝር መሠረት ከዚህ በታች በተጠቀሱ አካባቢዎች ላይ ማስገንባት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የሳይት ስም |
ፕሮጀክት |
ደረጃ |
የጨረታ ማስከበሪያ (ብር) CPO |
የግዥ መለያ ቁጥር |
|
1 |
ቅዱስ ሚካኤል |
የጎርፍ መሄጃ ቦይ |
GC-5 እና ከዚያ በላይ |
120,000 |
DILLA/UIIDP/ CW/018/25/26 |
|
2 |
ጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እስከ ነጭ አፈር |
የመንገድ መብራት ሪሎኬሽን (ቦታ መቀየር) |
ኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሪክ ዝርጋታ ሥራ ተቋራጭ EEM-5 ከዚያ በላይ |
150,000 |
DILLA/UIIDP/ CW/013/25/26 |
ከተጠቀሰውና ከዚያ በላይ ደረጃ ያላቸውን ኮንትራክተሮች ሆነው ስለዚህ ከዚህ በታች የቀረበውን መሥፈርት የሚያሟሉ ተቋራጮች መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
2. የተጨማሪ እሰት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
3. የንግድ ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
4. የአቅራቢነት ምዝገባ ም/ወረቀት ያላቸው
5. ከዘመኑ ግብር ዕዳ ነጻ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የምችሉ
6. የግንባታ ብቃት ማጋገጫ የምስክር ወረቀት ከኮንስትራክሽን ባለሥልን ማቅረብ የሚችሉ እና ሌሎች ለደረጃው የብቃት ማረጋገጫ እና ሚያስፈልጉ ማስረጃዎችን የጨረታ ሠነዱን ሞልተው ሲያቀርቡ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
7. ለግንባታ የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎችን ሙሉ በሙሉ ራሱን ችሎ መስራት የሚችል
8. ተጫራቾች ለግንባታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት ጨረታው እስከምከፈትበት ዕለት ድረስ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
9. የሚሰራውን የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡
10. ዘግይቶ የመጣ ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ኦርጅናል 1 ቴክኒካል 2 ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ፋይናንሻል 1 ኦርጅናል እና 2 ፋይናንሻል ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በማሸግ በመጨረሻ ሁሉንም በአንድ እናት በኤንቨሎፕ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ አድራሻችውን በመሙላት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 ተከታታይ የሥራ ቀን ቆይቶ በ22ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 5:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የመ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጌዴኦ ዞን የዲላ ከተማ ፋይ/ፕላ/ልማ/መምሪያ
