Tender Detail

Tender Details


በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቂሊንጦ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቂሊንጦ ለሥራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎች አሸዋ፣ የአርማታ ጠጠር፣ የግንባታ ድንጋይ፣ የሃርኮር ድንጋይ፣ የዝግባ ጣውላ የአርማታ ብረት ባለ 10 እስታፍ ባለ 6 ብሎኬት ባለ 15 ላሜንትድ ሚድፋ ባለ 188 ቲክነስ 2240/1220 ሚሚ፣ ቆርቆሮ ባለ 28 ጌጀ፣ አጠና ወራጅ ባለ 12 ሚሚ፣ አጠና ማገር ባለ 6 ሚሚ፣ ኮሚርስቶ ባለ (3 ሚሚ 244/1220 ሚሚ፣ ሞራሌ 50 ሚሚ /70 ሚሚ/ ባለ 4 ሜትር ቁመት፣ ሞራሌ 40 ሚሚ/50 ሚሚ፣ ኤሊ ዜድ ብረት፣ የበር ሰረገላ ቁልፍ፣ ቶሪኖ ማጠፊያ መካከለኛ፣ አንተሬስት፣ የፕላስቲክ ቀለም፣ ሲሚንቶ፣ የግንብ አሸዋ፣ 02 ጠጠር፣ ገረጋንት፣ እርዳሽ፣ ተለጣፊ ማብሪያ ማጥፊያ፣ ተለጣፊ ሶኬት ሆልደር ባለ 36 ዋት ሎረሰንት አምፖል ባለ 18 ዋት፣ ሆለደር ባለ 18 ዋት እስታርተር ኤስ 10 ብሬከር ባለ 25 አምፔር፣ የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 4 የኤሌክትሪክ ገመድ ባለ 2.5 ኮኔክተር 150 አምፔር፣ ፓውዛ ባለ 200 ዋት፣ ሬዚስታንስ ባለ 09 እና 08 ናስትሮ፣ የሸክላ ባለ 58 ስፋት፣ ቦዲ ባለ 58 ስፋት፣ የተለያዩ የቧን እቃዎች፣ እና ብዛት ያላቸው የጥገና አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል። በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት።
  2. የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
  3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
  4. የመንግሥት /ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ ሁለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት። ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል።
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉምየመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  10.  ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ማዕከል የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ግንቦት 07 ቀን 2018 . እስከ 500 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንክ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል።
  11. ጨረታው ግንቦት 07 ቀን 2018 . ከቀኑ 530 ሰዓት ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
  12.  የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል።
  13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም
  14. መሥሪያ ቤቱ የተ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ዝግ (የዓመት በዓል) ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር / ሳይንስና ቴከኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- 011 4 71 63 33 / 011 8 88 60 89/ 011 4 34 89 86 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

 

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል /ማረ/ቤት አስተዳደር/ ቂሊንጦ

Save Tender