በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ለጅማ ወለኔ ማ/ቤት በማ/ቤቱ በጀት ለሚያሰራው አዲስ የቄራ ግንባታ እና የማዘጋጃ ቤት ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር GGWW/21/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት በገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ለጅማ ወለኔ ማ/ቤት በማ/ቤቱ በጀት ለሚያሰራው አዲስ የቄራ ግንባታ እና የማዘጋጃ ቤት ጥገና ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
- የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
- የኦን ላይን E-TRADE ተመዝጋቢ መሆናቸውንና ከገቢዎች መስሪያ ቤት የኦዲት ክሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5% ተቀናሽ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ህጋዊ መታወቂያ ይዘው መምጣት አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ገ/ጉ/ወ/ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ብር 75,000 (ሰባ አምስት ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማደረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሀያ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ ከቀኑ 8፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፤ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
- በወረዳው ወስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም።
- ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅደመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራው መስራት የሚችሉ መሆን።
ለበለጠ መረጃ ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 011 336 06 31/146 ይደውሉ
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
መሀል አምባ
