Tender Detail

Tender Details

  • Company አዲስ አበባ ከተማ አውቶስ አገልግሎት ድርጅት
  • Address , Phone: 0118-21-22-14
  • Website
  • Deadline22 May 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • opening date2026-05-22 10:30:00
  • Categories Vehicle (Garage Service)

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቀላል ተሽከርካሪ ኢንጀክሽን ፓምፕ፣ ኢንጀክተር ኖዝል፣ ሲሊንደር ሄድ እና ሲሊንደር ብሎከ የጥገና አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ በግዥ መለያ ቁጥር ከአአድ/ብግጨቁ/040/2018 ለአንድ ዓመት የሚቆይ የቀላል ተሽከርካሪ ኢንጀሽን ፓም ኢንጀክተር ኖዝል፣ ሲሊንደር ሄድ እና ሲሊንደር ብሎከ የጥገና አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1.     በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee)!

2.     በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣

3.     የታ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT Certificate)

5.     በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)

6.     የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡

በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (600 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው /ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ወይም 7-01 መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 . ጠዋት 400 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ግንቦት 14 ቀን 2018 . ጠዋት 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ይከፈታል፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ስልክ ቁጥር፡- 0118 21 22 14

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender