Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል
  • Address መልካሣ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0222250216
  • Website
  • Deadline06 Jun 2026, 1:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • opening date2026-06-06 13:30:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል የወፍ መከላከያ ጎጆ Bird Impending Net " ግንባታ ሥራ ለማከናወን ማዕከሉ የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በማቅረብ የባለሙያ የእጅ ዋጋ (labor cost) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግ.ጨ 05/2018

 

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል የወፍ መከላከያ ጎጆ Bird Impending Net " ግንባታ ሥራ ለማከናወን ማዕከሉ የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በማቅረብ የባለሙያ የእጅ ዋጋ (labor cost) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

1.     በጨረታው ለመሳተፍ በዘርፉ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ማዕከ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

2.     የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3.     የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ ያሉ G.C እና BC የሥራ ተቋራጭ የሆኑ የግንባታ ሥራ ፍቃድ ያላቸው እና የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5.     ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት የግብር ግዴታቸውን መወጣታቸውንና ለ2018 በጀት ዓመት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ። ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች ማዕከሉ ለማሰራት የፈለገውን የግንባታ ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 (ሃያ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ከ2፡ዐዐ ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተመሰከረ CPO ወይም Un conditional bank guarantee for 90 calendar days from the bid opening date. (ያልተገደበ የባንከ ዋሰት) በማስያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአዳማ ከተማ ወደ አሰላ ከተማ በሚወስደው መንገድ 17 ኪ.ሜ በሚገኘው መልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል ከግዥና ፋይናንስ ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ) በመግዛትና የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ግልፅ ጨረታ ግጨ 05/2018 የመጫረቻ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ተለይቶ በህግና ደንብ መሰረት ታሽጎ መግባት ይኖርበታል።

ጨረታው ለ20 (ሃያ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ክፍት ሆኖ በ20ኛው ቀን ከቀኑ በ7፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልፅ ይከፈታል።

ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የበዓላት ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የጨረታው መክፈቻ ቀን ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል።

ዘግይተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ፡-

በስልክ ቁጥር +251 22 225 0216 የቢሮ እና በ09 11 94 26 50: በ09 11 03 57 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። 

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል

Save Tender