የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለክረምት ለፋብሪካችን ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MSF/LP/06/2026
የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለክረምት ለፋብሪካችን ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ጥቅል አንድ፡- Sheet Metals
ጥቅል ሁለት፡- Bolt & Nut
ጥቅል ሶስት፦ Electrical Materials
ጥቅል እራት፡- Grinding machine, carbon brush, wire brush; Spanners, Cutting disc, Cotter pin & others
ጥቅል አምስት፡- Bearing (ናሙና ይቅረብ)
ጥቅል ስድስት፡- Electrode (ናሙና ይቅረብ)
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባችኋል።
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ጥቅል ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም የባንክ ዋስትና /Bid bond guarantee/ በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.አ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንፃ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በዕለቱ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል
7. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-011 550 5607, 011 550 5633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሃራ ስኳር ፋብሪካ
