አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የተበዳሪው
ስም |
የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪ ቅርንጫፍ | የንብረቱ አድራሻ | የቦ(ው ስፋት (ሜ2) | የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት | የንብረቱ አይነት | የጨረ( መነሻ ዋጋ | ጨረ(ው የሚከናወንበት ቦታ፣ ቀን (ና ሰዓት | |||
| ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቤ.ቁ | |||||||||
| 1 | ወ/ሮ ፈቲያ ሰዒድ ዑመር | ወ/ሮ ፈቲያ ሰዒድ ዑመር | የካ | አዲስ አበባ | ቦሌ | 03
|
— | 546 | AA000060301141 | G+1 ቴራስ ያለው መኖሪያ ቤት | 63,459,596.05 | ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚካሄደው 22 አካባቢ በሚገኘው ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል።
- የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለጊዜ 4፡00 – 5:30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባው ከተጠናቀቀበኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
- በጨረታው የተሻለዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
- የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናትውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል፡፡
- በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው፡፡ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
- ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
- ከሚሸጠው ንብረትጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው የሊዝ ክፍያዎች፣ የካፒታል ጌይን ታክስ፣ ተ.እ.ታን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም የግብር ክፍያዎች እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ የአሹራ፣ የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።
- ባንኩ የተሻለመንገድ ካገኘ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝትቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-71-20 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.
