አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ንብረቶቹ በሚገኙበት የባንኩ ቅርንጫፎችና እና ሰሜን ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንጻ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር 6ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ንብረቱን ለመግዛት የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፁ ላይ ካሰፈሩ በኋላ የጨረታ ማስከበሪያና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማያያዝ በስም በታሸገ ፖስታ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መካሄጃ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ጨረታው በሚካሄድበቸው ቦታዎች ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ አስመዝግበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በሰንጠረዥ በተገለጸው ቦታ ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 አስከ 5፡30 ይካሄዳል፡
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር ፣15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ገዢ ይከፍላል፡፡ የሊዝ ክፍያ ውል ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል፡፡
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አሲዞ መጎብኘት ወይም ማየት ይቻላል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912835245/011-126-4594/0918-778427 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፤
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተቁ |
የተበዳሪው ሙሉ ስም |
የመያዣ ሰጫው ስም |
የንብረቱ ዓይነትና (አገልግሎት) |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ
ዋጋ |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ቦታ |
1 |
ዳንዔል መብራቱ |
ተበዳሪው |
መኖሪያ ቤት |
400 |
57/34/1892 |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ መተሐራ ከተማ |
709,845.00 |
በድጋሚ |
ሚያዚያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም አ.አ ከተማ ሰሜን ሆቴል ጎን በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 6ኛፎቅ እና አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤ |
