Tender Detail

Tender Details


በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ባለቤት የሌለውን የተለያየ ንብረቶች(የውሃ ዕቃዎችን) በፍርድ ቤት ያስወሰነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክፍለ ከተማ ገንዘብ /ቤት ባለቤት የሌለውን የተለያየ ንብረቶች(የውሃ ዕቃዎችንበፍርድ ቤት ያስወሰነውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታዉ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

1.       ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።

2.       ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ መወዳደር ትችላላችሁ።

3.       ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።

4.       የጨረታ ስነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር ሲንቄ ባንክ ለካምንት ቁጥር 1064934721214 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ከገላን ከፍለ ከተማ ገቢዎች ወደ ደረሰኝ በማስቀየር የጨረታ ሰነድ ከክፍለ ከተማው ፋይናንስ መውሰድ ትችላላችሁ።

5.       ለሽያጭ የቀረበው ባለቤት የሌለውን የተለያዩ ንብረቶች (የውሃ ዕቃዎችን) የሚገኘው በገላን ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ የሚገኝ ስለሆነ በአካል በመጎብኘት የሚገዙበትን ዋጋ በተዘገጀው የጨረታ ሰነድ መሙላት ይችላሉ።

6.       ተጫራቾች የቀረበው ባለቤት የሌለውን የተለያዩ የውሃ ዕቃዎችን ለመግዛት ያሸነፉትን ገንዘብ 10 ቀን ውስጥ /ቤቱ ባዘጋጀው ባንክ ገቢ በማድረግ ያሸነፈውን ማዕድን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማንሳት የሚችል መሆን አለበት።

7.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከዋጋ ማቀረቢያ ጋር ማቅረብ አለበት።

8.       የጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ቦኋላ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰዉ ቀን 430 የሚከፈት ሆኖ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።

9.       ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።

10.   መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጫረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.   የጨረታው መነሻ ዋጋዎች እና ሌሎች መረጃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልፆዋል።

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 23 57 49 41 / 09 40 57 40 98 / መጠየቀ ይችላሉ።

 

የገላን /ከተማ ገንዘብ /ቤት

Save Tender